• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 12 months ago
  • 403 Views

የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ መልዕክት

"ኢንዱስትሪ ፓርኮች በለሙባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚነታቸው ተጠናክሮ የሚቀጥልበት አግባብ ላይ እየተሰራ ነው" - ሽፈራው ሰለሞን

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ሰለሞን ኢንዱስትሪ ፓርኮች በለሙባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚነታቸውን ለማስቀጠልና ዘላቂ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል።

ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህን የገለፁት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እና ዩኤስ አይዲ በጋራ ያዘጋጁት ለጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የግብርና ምርቶች አቅርቦትን ማጎልበትና የግብዓት ትስስርን ይበልጥ ለማቀላጠፍ ያለመ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ በጅማ ከተማ ሲካሄድ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት ነው።

በተጨማሪም በመልዕክታቸው የጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሲገነባ ለአካባቢው ወጣቶች ሰፊ የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው ማድረጉን አንስተው አሁን ላይ ደግሞ ጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የግብርና ምርቶችን ማቀነባበር ላይ ያለውን እምቅ አቅም በመገንዘብ፤ በዘርፉ የተሰማሩ አምራች ባለሀብቶችን ወደ ፓርኩ በማስገባትና በአካባቢው ከሚገኙ አርሶአደሮች ጋር ሰፊ የገበያ ትስስር በመፍጠር ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ ስራ እየተከናወነ መሆኑን አሳውቀዋል።

አያይዘውም ከዩኤስ ኤድ ፕሮጀክቶች ጋር በቅንጅት በመስራት በጅማ ዞንና በአካባቢው ያሉ አርሶአደሮች ተጠቃሚነታቸው ዘላቂ እንዲሆንና በጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኙ አምራቾችም በቂ የምርት ግብዓት እንዲያገኙ ለማድረግ እንቅስቃሴዎች መጠናከራቸውን በመልዕክታቸው አረጋግጠዋል።