• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 2 months ago
  • 892 Views

የኮርፖሬሽኑ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በሀገር አቀፍ የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ኤግዚቢሽን

የኮርፖሬሽኑ ኃላፊዎችና ሰራተኞች የሀገር አቀፍ የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ኤግዚቢሽንን ጎበኙ

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከተለያዩ መምሪያዎች የተውጣጡ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በቱሪዝም ሚኒስትር አዘጋጅነት በሳይንስ ሙዚየም በተዘጋጀው የኢትዮጵያን እምቅ የቱሪዝም ፀጋዎች ለማስተዋወቅና የቱሪዝም ዘርፍ ለሃገር እድገት የሚያበረክተውን ፈርጀ ብዙ አስተዋጽኦ ለማስገንዘብ በተዘጋጀው ኤግዚቢሽን ላይ ተገኝተው ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በኤግዚቢሽኑ የኢትዮጵያን ምድረ ቀደምትነት የሚመሰክሩ ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊና፣ ባህላዊ የቱሪዝም ሃብቶችን የሚያሳዩ፣ በዘርፉ የተሰማሩ አካላት የሚሰጧቸውን ምርትና አገልግሎቶች የሚያስተዋውቁ እንዲሁም የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን አሁናዊና እና የወደፊት ጉዞ የሚያሣዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሚሳተፉበት ነው፡፡

“ቱሪዝም ለአረንጓዴ ልማት” በሚል መሪ ቃል በቱሪዝም ሚኒስቴር አዘጋጅነት ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 28 ለ30 ተከታታይ ቀናት በሚቆየው የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ኤግዚቢሽን የክልል ቱሪዝም ቢሮዎች፣ የቱሪስት አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች፣ የዘርፉ ባለሙያዎች፣ ሆቴሎች እንዲሁም የቴክኖሎጂ ባለሙያወች የሚሳተፉበት መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡