ኤች ቢኤም ግሩፕ በቀን ከ1 ሚሊዮን በላይ ሲሪንጆችን የሚያመርት ኩባንያ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሊገነባ ነው
ኤች ቢኤም ግሩፕ የተሰኘ የቻይና የፋርማሲዩቲካል ኩባንያ በቀን ከ1 ሚሊዮን በላይ ሲሪንጆችን በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለማምረት መወሰኑን ለኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አሳውቋል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የኤች ቢኤም ግሩፕ ባለቤትና ፕሬዚዳንት ከሆኑት ሚስተር ጎርደን ጋር በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ኮርፖሬሽኑ ገንብቶ ከሚያስተዳድራቸው የኢንቨስትመንት ማዕከሎች ውስጥ ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ አለም ላይ ካሉ ምርጥና ተወዳዳሪ የፋርማሲዩቲካል ማዕከሎች አንዱ መሆኑን ለግሩፑ ልዑካን ያስረዱት ዋና ስራ አስፈፃሚው አክሊሉ ታደሰ ኢንቨስትመንቱ ከፍተኛ የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግር እንዲኖርና ኢትዮጵያ በዘርፉ ከውጪ የምታስገባውን የህክምና ቁሳቁስ በሀገር ውስጥ ለመተካት የሚደረገውን ጥረት የሚደግፍ መሆን እንዳለበት አፅንኦት ሰጥተዋል።
የኤች ቢኤም ግሩፕ ባለቤትና ፕሬዚዳንትና ሚስተር ጎርደን በበኩላቸው በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና በአፍሪካ የመጀመሪያ የሚሆነውን የግሩፑን የሲሪንጅ ማምረቻ ለመገንባትና በቀን ከ1 ሚሊዮን እንዲሁም በዓመት ከ300 ሚሊዮን በላይ ሲሪንጆችን ለማምረት እንዳቀዱ አሳውቀዋል።
የልዑክ ቡድኑ አባላት ከዚህ ቀደም በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በጉብኝታቸውም በቂሊንጦ ኢንዱስሪ ፓርክ የተመለከቱት የመሰረተ ልማትና የአገልግሎት አቀራረብ እንደሳባቸውና ለውሳኔ እንደረዳቸው በመድረኩ ገልጸዋል፡፡
ኤች ቢኤም ግሩፕ እ.ኤ.አ በ1996 ተመስርቶ መቀመጫውን በአሜሪካ ኒውዮርክ ከተማ ያደረገ የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶችን የሚያመርት ሲሆን በቻይናም በዘርፉ መሪ የሆነና ምርቶቹን ለአለም ገበያ የሚያቀርብ ግዙፍ ኩባንያ ነው። ኩባንያው ከኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ጋር ላለፉት ስምንት ዓመታት በቅንጅት እየሰራና ምርቶቹን ከ100 በላይ ለሚሆኑ የአለም ሀገራት ኤክስፖርት እያደረገ ይገኛል።
HBM Group is going to build a company that will produce 1 million syringes per day in Kilinto Industrial Park
HBM Group, a pharmaceutical company, has informed the IPDC that it has decided to manufacture 1 million syringes per day at Kilinto Industrial Park.
IPDC CEO, Aklilu Tadesse, received Mr. Gordon, the owner of HBM Group, in his office and spokes to him.
Among the investment centers built and managed by the corporation, Kilinto Industry Park is one of the best and most competitive pharmaceutical centers in the world, Aklilu Stated. And He emphasized that the investment should support the efforts of Ethiopia to replace the imported medical equipment in the country in order to have a high level of technology and knowledge transfer.
Mr. Gordon, the owner of HBM Group, announced that he plans to build a world-class syringe factory in Kilinto Industrial Park, the first in Africa, and to produce more than 1 million syringes per day and 300 million plus per year.
The members of the delegation had previously visited Kilinto Industrial Park and they stated that they were attracted by the infrastructure and service approach they saw in the Park and that helped them to make the decision.
HBM Group was founded in 1996 and is headquartered in New York City, USA. It is a giant company that manufactures various medical equipment and is a leader in the field in China. The company has been cooperating with the Ethiopian Pharmaceuticals Supply Agency ( EPSA ) for the past 8 years and is exporting its products to more than 100 countries around the world.