• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 11 months, 1 week ago
  • 375 Views

ቻይና ተጨማሪ መዋዕለ ንዋይ በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች

ቻይና ተጨማሪ መዋዕለ ንዋይ በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ፈሰስ እንደምታደርግ ተገለፀ

ይህ የተገለፀው ኢትዮጵያ የአሥር ዓመት የልማትና የአገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ዕቅዷን ከቻይና "ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ" ጋር አሰናስላ እና አስማምታ ለመፈፀም መስማማቷን በአዲስ አበባ የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ ትናንት ጥቅምት 06 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ነው።

በመግለጫው ኢትዮጵያ የልማት እቅዶቿን ከ "ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ" ጋር በማሳለጥ ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንደምታገኝ የተገለፀ ሲሆን፣ ቻይና ተጨማሪ መዋዕለ ንዋይ በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ( Special Economy Zones ) ፈሰስ እንደምታደርግ በስምምነቱ ተገልጿል ተብሏል።

ሁለቱ ሀገራት ስምምነቱን ያከናወኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ( ዶ/ር ) አስረኛ አመቱ እየተከበረ ባለው የቻይና "ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ" ላይ ለመሳተፍ ቤጂንግ ከደረሱና ከፕሬዚዳንት ዢን ፒንግ ጋር ትናንት ከተገናኙ በኋላ ነው።

China will invest more in industrial parks and special economic zones - Chinese Embassy in Addis Ababa

This was stated in the statement issued by the Chinese Embassy in Addis Ababa on October 6, 2016 E.C that Ethiopia has agreed to facilitate and harmonize its ten-year development and indigenous economic reform plan with China's "Belt and Road Initiative".

In the statement, it was stated that Ethiopia will gain multifaceted benefits by streamlining its development plans with the "Belt and Road Initiative", and China will invest more in industrial parks and Special Economic Zones.

The two countries made the agreement after Prime Minister Abiy Ahmed (Dr.) arrived in Beijing to participate in the tenth anniversary of China's "Belt and Road Initiative" and met with President Xi Jinping