• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 2 months ago
  • 908 Views

በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አዳዲስ የደቡብ ኮሪያ ባለሀብቶች

"በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አዳዲስ የደቡብ ኮሪያ ባለሀብቶች ኢንቨስት እንዲያደርጉ ይሰራል" አክሊሉ ታደሰ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በኢትዮጵያ ከደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ካንግ ሲዩኪሄ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ የተካሄደው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውንና ለረጅም አመታት የዘለቀውን ግንኙነት ይበልጡኑ በቢዝነስና በኢንቨስትመንት ለማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ነው።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በኢትዮጵያ እና በደቡብ ኮሪያ መካከል ያለው ነባር ግንኙነት በደምና በአጥንት ጭምር መሰረት ያለው መሆኑን ጠቅሰው ይህንንም ይበልጡኑ ለማጠናከር በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ አፅንኦት ሰጥተዋል። አክለውም በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በተለያዩ ዘርፎች በተለይም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አዳዲስ የደቡብ ኮሪያ ባለሀብቶች ኢንቨስት እንዲያደርጉ ለማስቻል ይበልጥ ተቀራርቦ መስራት እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ካንግ ሲዩኪሄ

በኢትዮጵያና በደቡብ ኮሪያ መካከል ያለው ግንኙነት ከታሪክ ባሻገር ወደ እድገት ፤ ልማትና ኢንቨስትመንት ትብብር ማደግ እንዳለበት አንስተው በቀጣይም በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች በመሳተፍ ከኢትዮጵያ ጋር በዘርፉ ዋነኛ አጋር ሆነው መቀጠል እንደሚሹ አሳውቀዋል።

በውይይቱ መሰረትም በኢንቨስትመንትና ቢዝነስ፤ በስልጠናና በትምህርት መስኮች እንዲሁም በሌሎች መሰል የአጋርነት ዘርፎች በቅንጅት ለመስራት ከስምምነት ተደርሷል።

Efforts will be going To further strengthen the strong relationship between Ethiopia and South Korea through business and investment

IPDC CEO Aklilu Tadesse, discussed with South Korean Ambassador to Ethiopia Kang Seokhee.

The discussion was held on the issues that can be done to strengthen the long-standing relationship between the two countries through business and investment.

IPDC CEO Mr AKlilu mentioned that the existing relationship between Ethiopia and South Korea is based on blood and bones and emphasized the need to work together to strengthen it. He added that working more closely will enable new South Korean investors to invest in various sectors, especially in the manufacturing sector.

Ambassador of South Korea in Ethiopia, Kang Seokhee stated that the relationship between Ethiopia and South Korea goes beyond history; He mentioned that development and investment cooperation should grow and further he added that they would like to continue to be a major partner with Ethiopia by participating in various investment sectors in Ethiopia's industrial parks.

Based on the discussion, An agreement has been reached to work together in the fields of training and education as well as other areas of partnership.