• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 2 months ago
  • 970 Views

ሰንሻይን ኢትዮጵያ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ

ሰንሻይን ኢትዮጵያ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በፋርማሲዩቲካል ኢንቨስትመንት ዘርፍ የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከሰንሻይን ኢትዮጵያ ውል ቴክስታይል ፒኤልሲ ዋና ስራ አስኪያጅ ጋር ውይይት አድርገዋል።

አቶ አክሊሉ በውይይቱ ሰንሻይን በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ በጋርመንት ዘርፍ ተሰማርቶ በስራ እድል ፈጠራ፤ በውጭ ምንዛሬ ግኝት እንዲሁም በቴክኖሎጂ ሽግግር ውጤታማ ስራ በመስራት ላይ የሚገኝ መሆኑን አንስተዋል። አክለውም አሁን ላይ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ኢንቨስት ለማድረግ ያሳየውን ፍላጎት አድንቀው በአጭር ጊዜ ወደ ስራ እንዲገባ አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል ይደረጋል ብለዋል።

ሰንሻይን ኢትዮጵያ ውል ቴክስታይል ፒኤልሲ በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ በጋርመንት ኢንዱስትሪ ዘርፍ ተሰማርቶ የሚገኝ ትልቅ ኩባንያ ሲሆን ምርቶቹን ለአውሮፓና አሜሪካ እንዲሁም ለሩቅ ምስራቅ ሀገራት በማቅረብ የውጭ ምንዛሬ ከማስገኘቱ በተጨማሪ ለበርካታ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድልን የፈጠረ የውጪ ኩባንያ ነው።

Sunshine Ethiopia expressed its desire to engage in the field of pharmaceutical investment in Kilinto Industrial Park

IPDC CEO Aklilu Tadesse, had a discussion with the General Manager of Sunshine Ethiopia wool Textiles Plc.

As Aklilu stated in the discussion, Sunshine engaged in the Garment and textile sector and created job opportunity for citizens at Adama Industry Park. He mentioned that the company is performing effectively in foreign exchange acquisition and technology transfer.

He added that he appreciated the interest shown by the company to invest in the pharmaceutical sector in kilinto industrial park and said that the necessary support will be provided to put into operation in a short time.

Sunshine Ethiopia Wool Textile Plc is a large company engaged in the garment industry sector in Adama Industrial Park. Besides earning foreign currency by providing its products to Europe, America and the Far East, it is a foreign company that has created permanent and temporary employment opportunities for many citizens.