• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 11 months, 2 weeks ago
  • 374 Views

በ47 ቢሊዮን ብር በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚተገበሩት የኦቪድ ግሩፕ ፕሮጀክቶች

ከ47 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ለሚተገበሩ የኦቪድ ግሩፕ ፕሮጀክቶች የቅድመ ኢንቨስትመንት ስራዎች ተጀመሩ 

ኦቪድ ግሩፕ ከ47 ቢሊዮን ብር በላይ ኢንቨስት በማድረግ በተለያዩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለሚተገብራቸው ፕሮጀክቶች የሚሆኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጀምረዋል። 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የኦቪድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዮናስ ታደሰን ስለ ቅድመ ዝግጅት ስራዎቹ በፅ/ቤታቸው አግኝተው አነጋግረዋል። 

በንግግራቸው ወቅትም ኦቪድ ግሩፕ ሰርቶ ያጠናቀቃቸውን፤ እየሰራቸው ያሉና ወደፊት ለመስራት በእቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ያለባቸውን በርካታ ፕሮጀክቶች አስመልክቶ ያዘጋጃቸውን ነጥቦች ለዋና ስራ አስፈፃሚው ያቀረበ ሲሆን በልዩነትም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ለሚተገብራቸው ኢንቨስትመንቶች ያዘጋጀውን እቅድ አቅርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል። 

አሁን ላይ ኦቪድ ግሩፕ ግዙፍ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ፕሮጀክቶች በአጭር ግዜ ሰርቶ በማጠናቀቅ የሚመሰገን መሆኑን የጠቆሙት የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ፕሮጀክቱ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ተግባራዊ ሆኖ ስራ እስኪጀምር ድረስ ያልተቋረጠ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል። 

ፕሮጀክቱ ከስምንት ወራት እስከ አንድ አመት ባለው ግዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ያሉት የኦቪድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዮናስ ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ወደ ተግባር ሲገባ ከ13 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል እንደሚፈጥርና በ67 ሄክታር የለማ መሄት እንደሚተገበር ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ኮርፖሬሽኑ ከኦቪድ ግሩፕ ጋር በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ለተገጣጣሚ ቤቶች የሚሆኑ ግብዓቶችን ማምረት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መወያየታቸው የሚታወስ ነው።