• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 11 months, 2 weeks ago
  • 400 Views

የኮርፖሬሽኑ አሰራሮችን ወረቀት አልባ የማድረግ ሂደት

በኮርፖሬሽኑ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ወረቀት አልባ ለማድረግና ወደ ዲጅታል ለመቀየር የሚያስችሉ ስራዎች በመተግበር ላይ ይገኛሉ፡፡

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የሚሰጡ አገልግሎቶችን ወረቀት አልባ ለማድረግ የተጀመረው የኦራክል ክላውድ ፊውዥን ኢአርፒ ሲስተም የ2ኛ ምዕራፍ ማስጀመሪያን አስመልክቶ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ የተገኙት የትራንፎርሜሽንና ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም ከተማ የኦራክል ኢአርፒ ሲስተም በኮርፖሬሽኑ ሊተገበሩ የታቀዱ የሪፎርም ስራዎችን የሚደግፍና ዓለም አቀፍ የአሰራር ስርዓትን ለመተግበር የሚያግዝ በመሆኑ ለስኬታማነቱ ሁሉም ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት አሳስበው ከሶፍትዌር አቅራቢው ኦራክል ድርጅት ጋር በምዕራፍ አንድ ላይ የተጀመረው "strategic partnership" ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንና በመጀመሪያው ምዕራፍ የታዩ ክፍተቶችን በመለየት በ2ኛው ምዕራፍ ለምንተገብረው ስራ በግብዓትነት መውሰድ ይገባል ብለዋል፡፡

የሚተገበረው ሲስተም በሰው ሃይል፣በፋይናንስና ግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያዎች ላይ የሚሰጡ አገልገሎቶችን ወረቀት አልባና ሙሉ ለሙሉ ዲጅታላይዝ ለማድረግ የታሰበ ሲሆን በመጀመሪያው ምዕራፍ ላይ ተተግብሮ ውጤታማ በመሆኑ በ2ኛው ምዕራፍ በሌሎች መምሪያዎች ላይ ለመተግበር ስራው በይፋ የተጀመረ ሲሆን ይህም የኮርፖሬሽኑን የዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትና የአሰራር ስርዓትን ለማዘመን እና ለማቀላጠፍ ትልቅ ሚናን ይጫወታል፡፡