• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 11 months, 2 weeks ago
  • 351 Views

የኢትዮ ቻይና ፍሬንድሺፕ ኮርፖሬሽን ኢንቨስተሮች

በኢትዮ ቻይና ፍሬንድሺፕ ኮርፖሬሽን ስር የሚገኙ አምራች ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ገብተው እንዲያመርቱ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ 

በጉዳዩ ላይ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከኢትዮ ቻይና ፍሬንዲሺፕ ኮርፖሬሽን ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቤቲ ዡ ጋር ተወያይተዋል። 

ዋና ስራ አስፈፃሚው ኮርፖሬሽናቸው ገንብቶ በሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ነፃ ንግድ ቀጠና ያሉ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎችንና አማራጮችን፤ ለአምራቾች የተዘጋጁ ምቹ መሰረተ ልማቶችን እና የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችን ለፕሬዚዳንቷ በዝርዝር አስረድተዋል። 

ፕሬዝዳንቷ በበኩላቸው ቻይናውያን ባለሀብቶቹ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ገብተው ማምረት እንዲችሉ ስራዎች እንደሚከናወኑ ገልፀው ለዚህም በጋራ መስራት እንደሚገባ አክለዋል። 

ፕሬዚዳንቷ በኢትዮ ቻይና ፍሬንድሺፕ ኮርፖሬሽን ስር ከ100 በላይ የሚሆኑ ቻይናውያን አምራች ባለሀብቶችን የሚወክሉ ሲሆን ባለሀብቶቹም በአውቶሞቢል፤ በማሽነሪ፤ በአግሮ ፕሮሰሲንግ እና በሌሎችም የማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ናቸው። 

በውይይቱ ወቅት ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያካተተ ግዙፍ የኢንቨስትመንት ፎረም በቻይና ሀገር ለማዘጋጀት ከስምምነት ተደርሷል። 

A discussion was held to enable investors under the Ethio-China Friendship Corporation to enter and produce in industrial parks. 

IPDC CEO Aklilu Tadesse, discussed the matter with Betty Zhou, President of Ethio-China Friendship Corporation Committee. 

The CEO brief the investment activities and options in the industrial parks and free trade zones that IPDC builds and manages; He explained to the President in detail the favorable infrastructure and investment incentives for manufacturers. 

On her part, the president said that works will jointly be done so that the Chinese investors can enter and produce in the industrial parks, adding that they should work together for this. 

The president represents more than 100 Chinese manufacturing investors under the Ethio-China Friendship Corporation, and the investors are engaged in automobile, machinery, Agro-processing and other manufacturing sectors. 

During the discussion, an agreement was reached to jointly organize a huge investment forum in China that includes all stakeholders.