• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 11 months, 3 weeks ago
  • 341 Views

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ መልዕክት

ኢንዱስትሪያላይዜሽንን እውን ከማድረግ ሀገራዊ ሀላፊነት በተጨማሪ ለህዝባችን የሚጠቅሙ ህዝባዊ ፕሮጀክቶችን ማሰብ እና መተግበር የጋራ ግዴታችን ነው - አክሊሉ ታደሰ 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ኢንዱስትሪያላይዜሽንን እውን ከማድረግ ሀገራዊ ሀላፊነት በተጨማሪ ለህዝባችን የሚጠቅሙ ህዝባዊ ፕሮጀክቶችን ማሰብ እና መተግበር የጋራ ግዴታችን ነው ሲሉ ገልፀዋል። 

ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህን ያሳወቁት በትናንትናው እለት ኮርፖሬሽናቸው በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ አማካኝነት በአዳማ ከተማ በቦኩ ሸነን ቀበሌ ለሚያስገነባው የህዝብ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ ባስቀመጡበት ወቅት ነው። 

አክሊሉ ታደሰ በእለቱ ንግግራቸው ትምህርት ቤቶች መሰረታዊ እውቀት ብቻ ሳይሆን የሀገር ፍቅር የሚገነባባቸው መሆን እንደሚኖርባቸው አሳውቀው በለዉጡ መንግስት የተለማመድናቸዉ ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ጀምሮ በጥራት የማጠናቀቅ አዲስ እሳቤ በዚህም ማህበራዊ ፋይዳዉ ጉልህ በሆነዉ ፕሮጀክታችን ላይ እንደሚተገበር ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ብለዋል። 

መሰል ማህበራዊ ኃላፊነታችንን የምንወጣባቸው ፕሮጀክቶች በመላው ሀገሪቱ ገንብተን በምናስተዳድራቸው የኢንቨስትመንት ማዕከሎቻችን እውን የማድረግ እንቅስቃሴያችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው ፕሮጀክቱ እንዲጀመር ጥረት ላደረጉ ሁሉም አካላት ምስጋና አቅርበው በቀጣይም ፕሮጀክቱ በመጪው የአንድ አመት ግዜ ውስጥ ተጠናቆ ተማሪዎች የትምህርት ገበታቸው ላይ እስኪገኙ ድረስ ያልተቋረጠ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።