• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 11 months, 3 weeks ago
  • 342 Views

በኢትዮጵያ የማላዊ ኤምባሲ

ኢትዮጵያ በኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት በአጭር ግዜ ያካበተችው ልምድ ለማላዊ ኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት አይነተኛ ግብዓት ነው - በኢትዮጵያ የማላዊ ኤምባሲ 

ኢትዮጵያ በአጭር ግዜ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባትና በማልማት ያላት ከፍተኛና የካበተ ልምድ ማላዊ ለምታስበው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታና ልማት አይነተኛ ግብዓት እንደሚሆን በኢትዮጵያ የማላዊ ኤምባሲ ተወካይ ኢቫንስ ቺሳሱላ ገልፀዋል። 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የትራንስፎርሜሽንና ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም ከተማ በኢትዮጵ ከማላዊ ኤምባሲ ተወካይ ኢቫንስ ቺሳሱላ ጋር ውይይት አካሂደዋል። 

በውይይታቸውም ኮርፖሬሽኑ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባትና በማልማት እንዲሁም በማስተዳደር ያካበተውን ልምድ መሰረት በማድረግ በማላዊ የሚታሰበውን ይህንኑ ልማት እውን ለማድረግ ግብዓት የሚሆኑ ዝርዝር ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን በዘርፉ ከማላዊ መንግስት ጋር በቅርርብ ለመስራትም ከስምምነት ደርሰዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ በዘርፉ ከ40 ዓመታት በላይ ልምድ ያለው የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ከማላዊ መንግስት የሚመጡ ጥያቄዎችን ለማስተናገድ ከምንግዜውም በላይ ዝግጁ መሆኑን አቶ ፍፁም አረጋግጠዋል። 

የልዑክ ቡድኑ አባላት በሀዋሳ እና በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ያደረጉት ምልከታ ኢትዮጵያ ያካበተችው ልምድና በአጭር ግዜ ያስመዘገበችው ውጤት ለማላዊ እንዲሁም ለሌሎች መሰል የአፍሪካ ሀገራት የኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት አይነተኛ ግብዓት የሚሆኑ ዘርፈ ብዙ ልምዶች እንደሆኑ አስቀምጠዋል።