• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 11 months, 3 weeks ago
  • 339 Views

የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና

የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና በ2015 በጀት ዓመት ከ10.7 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማስገኘቱ ተገለፀ 

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ከ10.7 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጪ ምንዛሪ ማስገኘቱንና በቀጠናው መዋዕለ ንዋያቸውን ፈሰስ ማድረግ የሚፈልጉ የውጭ ባለሃብቶች ቁጥር እያደገ መምጣቱን የቀጠናው ሥራ አስኪያጅ አቶ ካሚል ኢብራሂም ተናግረዋል። 

ሥራ አስኪያጁ እንደ ሀገር የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ነፃ ንግድ ቀጠናው አይነተኛ ሚና ይጫወታልም ብለዋል። 

ቀደም ሲል የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ የነበረው ወደ ነፃ የንግድ ቀጠና ከተለወጠ ወዲህ መዋዕለ ንዋያቸውን ፈሰስ ማድረግ የሚፈልጉ የውጭ ባለሃብቶች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ገልጸዋል። 

በቀጠናው የተገነቡ 15 ሼዶች ሙሉ በሙሉ በውጭ እና የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች በአሁኑ ወቅት ተይዘው መጠናቀቃቸው ነፃ የንግድ ቀጠናው ያመጣው ውጤት መሆኑን ስራ አስኪያጁ አክለዋል። 

ከውጭ ሀገራት በምንዛሬ የሚገቡ ምርቶችን በንግድ ቀጠናው በማምረት የውጭ ምንዛሬን ማዳን እንደተቻለ ጠቁመው÷ በዘንድሮ ዓመት ብቻ ከ1 ሺህ በላይ ዜጎች በድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና የሥራ ዕድል ማግኘታቸውን ገልጸዋል። 

በቀጣይም የነፃ ንግድ ቀጠናውን በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ለማስገባትና ለልማት የሚኖረውን አበርክቶ ዕውን ለማድረግ የሚያስችል የነፃ ንግድ ቀጠናዎች አዋጅ ዘንድሮ ይወጣል ተብሎ እንደሚጠበቅም አመልክተዋል። 

አዋጁ በቀጠናው ሼድ የወሰዱ ባለሀብቶች በሙሉ አቅም ወደሥራ ለማስገባት የነበሩ የህግና የአሠራር ከፍተቶችን ለመፍታት የሚያስችል እንደሆነም ገልፀዋል፡፡ 

በተጨማሪም ነፃ የንግድ ቀጠናው አሁን እየሰጠ ካለው የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በተጨማሪ የሎጂስቲክ እና የንግድ ዘርፎችን ወደሥራ በማስገባት ልማቱን ለማፋጠን ያስችላል ብለዋል።