• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year ago
  • 399 Views

የአሜሪካው ኢስተርን ኮርፖሬሽን በኢንዱስትሪ ፓርኮች

የአሜሪካው ኢስተርን ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው ቤቶችን ለመገንባትና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ

በአገረ አሜሪካ በተለያዩ የኮንስትራክሽን ዘርፎች ላይ የካበተ ልምድ ያለው ኢስተርን ኮርፖሬሽን  ኩባንያ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለሚሰሩ ሰራተኞች በተመጣጣኝ ዋጋ ቤቶችን ለመገንባትና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገለፀ። 

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የትራንስፎርሜሽን እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም ከተማ ከኩባኒያዉ   ዋና ስራ አስፈፃሚ  ዴቪድ ሃምና ልዑካቸዉ  ጋር ተወያይተዋል ። 

በውይይቱ የትራንስፎርሜሽን እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ኃላፊው አቶ ፍፁም ከተማ ኢስተርን ኮርፖሬሽን በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢንቨስት ለማድረግና ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸዉን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለመገንባት ያሳየውን ከፍተኛ ፍላጎት አድንቀዋል።  

ኮርፖሬሽኑ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለውን የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት በከፍተኛ ሁኔታ ለመጨመርና አጠቃላይ የሰራተኛዉን ምቹ ሁኔታ ለመጠበቅ የሚያግዙ የሪፎርም ስራዎች በመሰራት ላይ መሆኑን ያነሱት አቶ ፍፁም ኩባንያው ወደ ስራ እንዲገባ አስፈላጊውን የድጋፍና ክትትል የማድረግ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡ 

የኢስተርን ኩባኒያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዴቪድ ሃም በበኩላቸው ኩባንያቸው በአሜሪካን ሃገር  በተለያዩ ግንባታዎች ላይ  ያካበተውን ልምድ በኢትዮጵያ ለማስፋፋት ማቀዱን ገልጸው  በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክም ኢንቨስት በማድረግ በዘርፉ የራሱን አሻራ ለማሳረፍ ማቀዱን አሳውቀዋል፡፡ 

ኢስተርን ኩባኒያ  በአሜሪካን ሃገር በኮንስትራክሽን ዘርፍ ከ25 ዓመታት በላይ  በቤቶች ግንባታ ፤  እንዲሁም በፕሮጀክት ማስተዳደር ዘርፍ ልምድ ያለው ሲሆን ከ2000 በላይ ግንባታዎችን በማጠናቀቅ ለደንበኞቹ ያስረከበ ግዙፍ ኩባንያ  ነው፡፡ 

Eastern Corporation expressed its desire to build affordable houses and engage in manufacturing in Ethiopia. 

Eastern Corporation, a company with extensive experience in the construction sector in the United States, expressed its desire to build affordable houses in Ethiopia's industrial parks and invest in the manufacturing sector. 

IPDC Chief of Staff Mr. Fitsum Ketema, had a discussion with the CEO of the American Eastern Corporation Company, David Ham. 

In the discussion, Mr. Fitsum appreciated Eastern Corporation's interest in investing in Kilinto Industrial Park. 

Mr. Fitsum mentioned that the corporation is working on reforms to increase the flow of foreign investment in the industrial parks. 

He additionally mentioned that IPDC is working on reforms to increase the flow of foreign investment in the industrial parks and confirmed that the necessary support will continue to be strengthened so that the company can start operation. 

Eastern Corporation CEO, David Ham, on his part, stated that his company plans to expand its experience in the construction of houses in the United States to Ethiopia, and announced that it plans to make its own mark in the sector by investing in Kilinto Industrial Park. 

Eastern Corporation is a giant company in the construction sector in the United States that has an experience of 25+ years in housing, construction of interior design and project management and is a huge company that has completed more than 2000 constructions and handed over to its clients.