በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ከ3 ግዙፍ የስኳር ፋብሪካዎች ጋር የውል ስምምነት ተፈራረመ።
የውል ስምምነቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከመተሃራ፣ወንጅ እና ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ስራ አስኪያጆች ጋር ተፈራርመዋል።
በውል ስምምነቱ ዋና ስራ አስፈፃሚው አክሊሉ ታደሰ ሶስቱ የስኴር ፋብሪካዎች የሀገር ባለውለታ እና የባንዲራ ፕሮጀክቶቻችን በመሆናቸው እነሱን ለማገዝ በመቻላችን ኩራት ይሰማናል ብለዋል።
የውል ስምምነቱ የስኳር ፋብሪካዎቹ ያጋጠማቸውን ምርት መቀነስና የምርታማነት ማሽቆልቆል ፤ የማሽነሪዎች ብልሽት እድሳትና ቅያሪ እንዲሁም ማስፋፊያዎቹን ታሳቢ በማድረግ በጥናት የተደገፈ ለፋይናንስ ምንጭ የሚሆን ዶክመንት የማዘጋጀትና ፋብሪካዎቹን ውጤታማ የሚያደርግ ጥናት ለመስራት የሚያስችል መሆኑን በስምምነቱ ተገልጿል።
በዛሬው እለት የስምምነት ፊርማ ያደረጉት የስኳር ፋብሪካዎች በሚኒስቴሮች ምክር ቤት ራሳቸውን ችለው እንዲቋቋሙ በተወሰነላቸው መሰረት በሙሉ አቅማቸው ወደስራ ለመግባት እየሰሩ ሲሆን አሁን ላይ ከ10ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል።
የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት በጥናትና ማማከር ላለፉት 40 ዓመታት በላይ የተለያዩ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን እውን ያደረገ ተቋም ሲሆን አሁንም ከግዙፍ መሰል ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ጋር ይበልጥ በጋራ እየሰራ ይገኛል።