የጃፓን ኢንተርናሽናል የልማት ተራድኦ ድርጅት(JICA) ኮርፖሬሽኑ እያከናወናቸው የሚገኙ የሪፎርም ስራዎች እንደሚደግፍ ገለፀ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አክሊሉ ታደሰ ከጃፓን ኢንተርናሽናል የልማት ተራድኦ ድርጅት ተወካዮች ጋር አብሮ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ የልማት ድርጅቱ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እየተሰሩ ያሉ የሪፎርም ትግበራ ስራዎች ዙሪያ ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን ኮርፖሬሽኑ እያከናወናቸው ያሉትን የሪፎርም ስራወችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የጃፓን ኢንተርናሽናል የልማት ድርጅት ከዚህ ቀደም በፓርኮች ልማት፣ በጥናትና ምርምር፣ በአካባቢ ጥበቃና ልማት እንዲሁም በበርካታ ጉዳዮች ላይ ከኮርፖሬሽኑ ጋር በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን በውይይቱ የተገለጸ ሲሆን በቀጣይም አጠናክሮ ማስቀጠል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
Japan International Development Cooperation Agency (JICA) stated that it supports the reform works being carried out by IPDC.
IPDC CEO, Aklilu Tadesse discussed with the representatives of JICA about issues they can work together with.
During the discussion, JICA was informed about the reform implementation works being done by IPDC and they expressed their commitment to support the reform works being carried out by the corporation.
In the discussion, it was revealed that JICA has been carrying out many activities with the corporation in the past in the development of parks, research, environmental protection and development as well as on many issues, and a mutual agreement was reached on the issues that can be strengthened in the future.