የኮርፖሬሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች በሀገራዊ የአስር ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ላይ ተወያዩ
ውይይቱ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት በአዲስ አበባ ተከናውኗል።
የእቅዱን ዝርዝር ማብራሪያ የኮርፖሬሽኑ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ሰለሞን እና የእቅድ እና ክትትል መምሪያ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ዘካሪያስ በጋራ በማቅረብ ውይይቱን መርተዋል።
በመድረኩ አጠቃላይ ሀገራዊ እቅድ እንዲሁም የኮርፖሬሽኑን ራዕይና ተልዕኮ የሚመለከቱ አበይት ክንውኖች ላይ ትኩረት በማድረግ ዝርዝር ሀሳቦች ቀርበው አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል።
በእቅዱ መሰረትም የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የ10 ዓመት ስትራቴጂክ እቅዱ ላይ በቀረበው ሀገራዊ እቅድ መሰረት ማሻሻያ እንደሚያደርግ ተጠቁሟል።