• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 3 months ago
  • 1031 Views

የአፍሪካ ሲንጋፖር ቢዝነስ ፎረም 2023

የአፍሪካ ሲንጋፖር ቢዝነስ ፎረም 2023 በሲንጋፖር መካሄድ ጀመረ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በጋራ የሚሳተፉበት የአፍሪካ ሲንጋፖር ቢዝነስ ፎረም 2023 በሲንጋፖር እየተካሄደ ይገኛል።

በፎረሙ ኢትዮጵያን በመወከል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሚ እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ኃላፊዎቹ በቆይታቸው ከተለያዩ አለም አቀፍ አምራቾችና ዲፕሎማቶች ጋር ውይይቶችን እያካሄዱ ሲሆን ይህም ለኢትዮጵያ አዲስ ኢንቨስትመንት በማምጣት በኩል ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል።

በመድረኩ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገር መሆኗ እንደ አንድ ትልቅ የኢንቨስትመንት እድል የተዋወቀ ሲሆን በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሉ አጠቃላይ የኢንቨስትመንት አማራጮች፤ የተዘጋጁ መሰረተ ልማቶችና የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችም ቀርበዋል።

Africa Singapore Business Forum 2023 has started to take place in Singapore

The Business Forum is being held in Singapore in which IPDC and EIC jointly participate.

Ethiopian Investment Commission Commissioner Lelise Nemi and Industrial Parks Development Corporation CEO Aklilu Tadesse are participating Representing Ethiopia in the forum.

The officials are holding discussions with various international manufacturers and diplomats during their stay, which is expected to play a significant role in bringing new investment to Ethiopia.

Ethiopia being a BRICS member country was introduced as a great investment opportunity in the forum. Additionally general investment options in Ethiopia's industrial parks; infrastructure and investment incentives are also presented.