• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 4 months ago
  • 1057 Views

የብራዚል ኩባንያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች

ስኳር ማቀነባበር ላይ የተሰማራ የብራዚል ኩባንያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ለማምረት ያለውን ፍላጎት ገለፀ

ኩባንያው ፍላጎቱን ያሳወቀው ተወካዩ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የትራንስፎርሜሽንና የዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም ከተማ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።

ኃላፊው ተወካዩን ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን ዝርዝር የኢንቨስትመንት ሀሳቡ ላይ ተወያይተው ኢንቨስትመንቱ በደብረ ብርሀን ኢንዱስትሪ ፓርክ እውን እንዲሆን ስራዎች እንደሚሰሩ ጠቁመዋል።

በውይይቱ ወቅት የኩባንያው ተወካይ ዝርዝር እቅዳቸውን ያቀረቡ ሲሆን ኩባንያቸው በጅቡቲ ስኳር ማቀነባበር ላይ እየሰራ እንደሚገኝና ያንንም በኢትዮጵያ ማስፋት እንደሚፈልግ አሳውቀዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በኢትዮጵያ የብራዚል አምባሳደር ከሆኑት ጃንዲር ፌሬራ ዶሳንቶስ ጋር በቅርቡ መወያየታቸው አይዘነጋም።

A Brazilian company engaged in sugar processing expressed its desire to produce in industrial parks

The company announced its interest when the representative had a discussion with IPDC Chief of Staff Mr. Fitsum Ketema.

Mr. Fitsum received and spoke to the representative and discussed the detailed investment idea and pointed out that works will be done to make the investment placed in Debre Birhan Industrial Park.

During the discussion, the representative of the company presented their detailed plan and informed that their company is working on sugar processing in Djibouti and wants to expand its business in Ethiopia.

Along with this, recently IPDC CEO Aklilu Tadesse, had a discussion with the Ambassador of Brazil to Ethiopia, Jandyr Ferreira Dos Santos.