"የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎትን በአፍሪካ ስመጥር እና ቀዳሚ ለማድረግ እንሰራለን" - የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ
ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህንን መልዕክት ያስተላለፉት በዛሬው እለት በተካሄደው የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት አገር አቀፍ ወርክሾፕ ላይ ነው።
ወርክሾፑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፤ አማካሪ ድርጅቶች፤ ዩኒቨርሲቲዎች፤ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት እና የፌደራልና የክልል አመራሮች በተገኙበት በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
ወርክሾፑን በይፋ ያስጀመሩት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከ40 ዓመታት በላይ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን በማማከር እና ጥናቶችን በመስራት እውቅና በማትረፍ ሲያገለግል የቆየዉን ተቋም በሚሰጠው አገልግሎት በአፍሪካ ስመጥር እና ቀዳሚ ለማድረግ የሚያስችል የሪፎርም ስራዎችን እያከናወንን ነው ብለዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ብቁ አደረጃጀት፤ የሰው ሀይልና ቴክኖሎጂን በመጠቀም አገልግሎቱ ያለውን ግዙፍ ልምድ በማጠናከርና አዳዲስ አሰራሮችንና ልምዶችን ተግባራዊ በማድረግ እድሜውንና አገሪቱ ከዘርፉ የምትጠብቀዉን ዉጤት ለማሳካት የሚመጠን ተመራጭ የስልጠናና ማማከር አገልግሎት ሰጪ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
በዛሬው እለት በተካሄደው አገር አቀፍ ወርክሾፕ ላይ ዘርፉን የሚመለከቱ ጥናታዊ ፅሁፎች፤ ሪፖርቶችና ልምዶች በምሁራን የቀረቡ ሲሆን ሰፊ የፓናል ዉይይት ተከናውኗል።
የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ከ40 ዓመታት በላይ በተለያዩ ዘርፎች የጥናትና የማማከር አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ጨምሮ የግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን ጥናት በማከናወን እውቅናን ያተረፈ ተቋም ነው።
"We strive to make industrial projects service leading in Africa" - CEO of the Corporation
The CEO conveyed this message at the National Workshop of Industrial Projects Services held today.
In the Workshop which was held in Addis Ababa, Ministry institutions, consulting Firms, Universities and various stakeholders
were attended.
IPDC CEO Aklilu Tadesse, who officially launched the workshop stated that IPS has gained recognition for over 40 years of consulting and conducting studies on large national projects. He added that IPDC is carrying out reform works to make the project services leading in Africa.
The CEO added that IPDC is working to strengthen the vast experience of the service by selecting competitive organizational structure, human resources and technology and implementing new procedures and practices to make it a leading training and consulting service provider.
At the national workshop held today, researches, reports and experiences related to the sector were presented by scholars and a panel discussion was also held.
Industrial Projects Service (IPS) has been providing research and consulting services in various fields for more than 40 years, and it is a service office that has gained recognition by conducting research on large national projects, including industrial parks.