• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 4 months ago
  • 1046 Views

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ ጋር በመተባበር በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የአውሮፕላን የውስጥ አካላትን ሊያመርት ነው

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አየር መንገዱ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የአውሮፕላን የውስጥ አካላትን ማምረት እንዲችል የስምምነት የፊርማ ስነ ስርዓት አከናውነዋል።

የፊርማ ስነ ስነ-ስርዓቱን ያከናወኑት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ፤ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እና የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዳንኤል ተሬሳ ናቸው።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ወቅት ስምምነቱ ከወትሮው የተለየ መሆኑን ገልፀው የኢትዮጵያውያን እና የመላው አፍሪካውያን ኩራት የሆነው አየር መንገዳችን መንገደኞችን ከመጓጓዝ አልፎ ወደ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በመሰማራቱና ይህ ኢንቨስትመንትም እንዲሳካ እገዛ በማድረጋችን ታላቅ ኩራት ይሰማናል ብለዋል። ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም ፕሮጀክቱ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ በቁርጠኝነት ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በበኩላቸው አየር መንገዱ ለሀገር ትልቅ ጥቅም ያለው ፕሮጀክት እውን እንዲያደርግ ላገዙ ሁሉ ምስጋና ይገባል ብለው ስምምነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን የውስጥ አካላትን ኢትዮጵያ ውስጥ እያመረተ ለአውሮፕላን አምራቾች በማቅረብ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ የሚያስገኝ መሆኑን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ፌዝ 2 ከ810 ሚሊዮን ብር በላይ ኢንቨስት በማድረግና 4 ሄክታር የለማ መሬት በመውሰድ የተለያዩ የአውሮፕላን የውስጥ አካላትን ለቦይንግ፣ ለኤርባስ እና ጣሊያን ሀገር ለሚገኝ የአውሮፕላን አምራች ኩባንያ እንደሚያቀርብ ተገልጿል።

Ethiopian Airlines, in cooperation with Boeing, is going to produce aircraft internal components at Kilinto Industrial Park

Industrial Parks Development Corporation with Ethiopian Airlines held an agreement signing ceremony to enable the production of aircraft internal components in kilinto Industrial Park.

The signing ceremony was performed by the Ethiopian Airlines CEO, Mesfen Tassew, IPDC CEO Aklilu Tadesse and Investment Commission deputy commissioner Daniel Teressa.

Aklilu Tadesse, IPDC CEO stated during the signing ceremony that the agreement was different from the usual one. He said that our airline, which is the pride of Ethiopians and all Africans, has gone beyond transporting passengers to the manufacturing sector and we are very proud to help make this investment a reality.

The CEO confirmed that IPDC will support the project with determination until it starts operation.

Ethiopian Airlines CEO, M.r Mesfin, in his part thanked all stakeholders who helped the airline to realize a project that has a great benefit to the country. He added, the agreement brought up Ethiopian Airlines to produce aircraft internal components in Ethiopia and provide airplane manufacturers, which will earn a lot of foreign exchange.

Ethiopian Airlines has invested more than 810 million birr in Kilinto Industrial Park phase 2 and taken 4 hectares of service land to supply various aircraft internal components to Boeing, Airbus and an Italian aircraft manufacturing company.