የብራዚል ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢንቨስት እንዲያደርጉና በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ አምራቾች ተጨማሪ ገበያ እንዲያገኙ ለመስራት ከስምምነት ተደረሰ።
የብራዚል አምራች ኩባንያዎች በኢንዱስትሪ ፓርኮች በተለይም በማኑፋክቸሪንግና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ እንዲሰማሩ እና በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚገኙ አምራቾች በብራዚል ተጨማሪ የገበያ መዳረሻዎችን እንዲያገኙ ለመስራት ከስምምነት ተደርሷል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በኢትዮጵያ የብራዚል አምባሳደር ከሆኑት ጃንዲር ፌሬራ ዶሳንቶስ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም ኢትዮጵያ እና ብራዚል በዘርፈ ብዙ መስኮች ለረጅም ዓመታት የዘለቀ ግንኙነታቸውን በኢንቨስትመንትና ተያያዥ ጉዳዮችም ማጠናከር በሚቻልባቸው ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።
በዚህም የብራዚል ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ እንዲያመርቱ እንዲሁም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚገኙ አምራች ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን በብራዚል ገበያ መሸጥ እንዲችሉና የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ ለማስቻል ከስምምነት ደርሰዋል።
በማኑፋክቸሪንግ በተለይም በአግሮፕሮሰሲግ ዘርፍ ብራዚል ያላትን ረጅም ልምድና ተሞክሮ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ስር ወዳሉ ኢንቨስትመንቶች ማስፋፋት በሚቻልባቸው እና ተጨማሪ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ዉይይት አካሂደዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ አምባሳደሩ አሁን ላይ በኮርፖሬሽኑ በኩል ያሉ እንቅስቃሴዎች አበረታች መሆናቸውን ገልፀው በተለይም ኢትዮጵያ በአግሮፕሮሰሲግ ዘርፍ ያላትን እምቅ አቅም በመጠቀም በዘርፉ ለተሰማሩ ኢንቨስትመንቶች በብራዚል ያለውን ተሞክሮ እንዲያገኙ ለማስቻል እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
በቀጣይም የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የቢዝነስ ፎረም በጋራ እንደሚሰናዳ ተጠቁሟል።
ብራዚል እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ያላት፣ በጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት በአለም 10ኛ እንዲሁም በመግዛት አቅሟ ደግሞ 8ኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ስትሆን በከፍተኛ ደረጃ በማደግ ላይ የሚገኝ መካከለኛና ቅይጥ ኢኮኖሚ ያላት ሀገር ናት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከብራዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማውሮ ቪዬራ ጋር በቅርቡ ተገናኝተው በኢትዮጵያ እና በብራዚል መካከል ግንኙነትን ስለማጠናከር እና በብዝኃ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸው አይዘነጋም።
An agreement was reached to allow Brazilian investors to invest in industrial parks and to allow manufacturers in industrial parks to access additional markets.
The agreement was reached for Brazilian manufacturers to engage in industrial parks, especially in the manufacturing and agro-processing sectors, and for producers located in industrial parks to find more market destinations in Brazil.
IPDC CEO Aklilu Tadesse, had a discussion with Jandyr Ferreira Dos Santos, the Ambassador of Brazil to Ethiopia.
In their discussion, they exchanged ideas on the details of how to strengthen the long-standing relationship of Ethiopia and Brazil in many fields through investment and related issues.
Thus, they reached an agreement to allow Brazilian investors to produce in industrial parks and manufacturing companies located in industrial parks to be able to sell their products in the Brazilian market and to create market linkages.
Brazil's long experience in manufacturing, especially in the agro-processing sector, can be expanded to the investments under IPDC and can attract more new investments.
In this regard, the ambassador stated that the current activities of IPDC are encouraging and that they will work to enable the investments in the sector to gain experience in Brazil by using Ethiopia's potential in the agro-processing sector
It was suggested that a business forum involving various stakeholders will be jointly prepared.
It is known that Prime Minister Abiy Ahmed (Dr.) recently met with Brazilian Foreign Minister Mauro Vieira and discussed strengthening relations between Ethiopia and Brazil and multilateral issues.