• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 4 months ago
  • 1069 Views

የቻይናው ኩባንያ CCECC በጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ

በቡና ማቀነባበር ላይ የሚሰማራ CCECC የተሰኘ የቻይና ኩባንያ በጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢንቨስት ለማድረግ ስምምነት ተፈራረመ

CCECC የተሰኘ የቻይና ኩባንያ ለአግሮ ፕሮሰሲንግ ምቹ ሆኖ በተገነባው ጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ በቡና ማቀነባበር ዘርፍ ለመሰማራት በዛሬው እለት የኢንቨስትመንት ስምምነት ፊርማ ተፈራርሟል። 

የፊርማ ስነ-ስርዓቱን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዳንኤል ተሬሳና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ሰለሞን ከCCECC ኩባንያ ተወካዮች ጋር በጋራ አከናውነዋል። 

ኩባንያው ለአግሮ ፕሮሰሲንግ ምቹ ሆኖ በተገነባው በጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢንቨስት በማድረግ በጅማ እና በአካባቢው በስፋት የሚገኘውን የቡና ምርት ማቀነባበር ላይ የሚሰማራ እንደሚሆን ተገልጿል። 

ከፊርማ ስነ-ስርዓቱ ባሻገር አምባሳደር ዣኦ፤ ክብርት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሚ እና አክሊሉ ታደሰ በኢንዱስትሪ ፓርኩ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል። 

ከአዲስ አበባ በ360 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በውቢቷ ጅማ ከተማ የሚገኘው ግዙፉ ጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የአግሮ ፕሮሰሲንግ ማዕከል ሲሆን አራት ባለ 5 ሺ 500 እንዲሁም አምስት ባለ 3 ሺ ሜትር ስኩዌር የማምረቻ ሼዶች መሰረተ ልማቶች ተገንብተውላቸው ጥንቅቅ ብለው ለአምራቾች አና ለባለሀብቶች ተዘጋጅተዋል፡፡                      

CCECC, a Chinese company engaged in coffee processing, signed an agreement to invest in Jimma Industrial Park. 

A Chinese company named CCECC has signed an investment agreement today to engage in coffee processing at Jimma Industrial Park, which was built to facilitate agro-processing sector. 

Daniel Teresa, Deputy Commissioner of Investment Commission and Shiferaw Solomon, Deputy CEO of IPDC jointly done the signing ceremony with CCECC company representatives. 

The company will invest in Jimma Industrial Park, which was built to be convenient for agro-processing sector, and will engage in coffe processing that are widely available in Jimma and the surrounding area. 

After the signing ceremony, Ambassador Zhao, Commissioner Lelise Nemi and Aklilu Tadesse done a green legacy program at the Industrial Park. 

Located 360 km from Addis Ababa in the beautiful city of Jimma, the huge Jimma Industrial Park is an agro-processing center, with four 5,500 square meter and five 3,000 square meter production sheds.