• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 4 months ago
  • 1149 Views

የአለም ባንክ ፕሬዚዳንት አጃይ ባንጋ የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ቆይታ

ኢትዮጵያ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ፤ በስራ እድል ፈጠራ እና በገበያ ትስስር እያስመዘገበች ያለው ለውጥ ተስፋ ሰጪ ነው - የአለም ባንክ ፕሬዚዳንት አጃይ ባንጋ 

ፕሬዚዳንቱ ይህንን የገለፁት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው ግዙፍ የኢንቨስትመንት ማዕከሎች አንዱ የሆነውን ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በጎበኙበት ወቅት ነው። 

ፕሬዝዳንቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በጋራ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኙ ጄይ ጄይ እና ሱፍሌ የተሰኙ ሁለት የጨርቃ ጨርቅና ብቅል አምራች ኩባንያዎችን የተመለከቱ ሲሆን በምልከታቸውም ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል። 

ፕሬዝዳንቱ ከጉብኝታቸው መጠናቀቅ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ በማኑፋክቸሪንግ፤ ለወጣቶችና ለሴቶች እየፈጠረች ባለችው የስራ እድል፤ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ባሉባቸው ቦታዎች ከአርሶ አደሮች ጋር የተፈጠረው የስራ እድል በዘርፉ እያስመዘገበች ያለችው ውጤት ተስፋ ሰጪ መሆኑን አረጋግጠዋል። 

ከጉብኝት መርሀ ግብሩ ባሻገር የአለም ባንክ ፕሬዚዳንቱ አጃይ ባንጋ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል። 

'Ethiopia's achievement in terms of job creation and market linkages is promising' - World Bank President Ajay Banga 

The President made this statement when he visited Bole Lemi Industrial Park, one of the huge investment centers managed by IPDC, together with Prime Minister Abiy Ahmed (Dr.). 

In the President's message after the end of his visit, The change in the manufacturing sector that Ethiopia is achieving in terms of job creation and market linkages in the places where industrial parks are located is promising. 

The President together with Prime Minister Abiy Ahmed (Dr.) visited two textile and malt manufacturing companies named Jay Jay and Souffle located in Bole Limi Industrial Park, , and expressed that he was happy with his tour. 

Apart from the tour program, the President of the World Bank, Ajay Banga, left his green footprint with Prime Minister Abiy Ahmed (Dr.).