• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 1 month ago
  • 348 Views

በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራው ልዑክ በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ  አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራ የልዑካን ቡድን በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ ክብርት አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራ ልዑክ እና የተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች እና ሰራተኞች በድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠና አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል ። 

በመርሃ ግብሩ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በአረንጓዴ አሻራ ያመጣነው ስኬት ሀገራችን ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ እና ጥበቃ እየሰራች ያለችው ተግባር ለመጭው ዘመን ትውልድ አኩሪ እና ለሌሎች ሀገራት በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል። 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ፤ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ሰራተኞች  የተለያዩ አምባሳደሮች ፤ ዲፕሎማቶች እና ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በነፃ ንግድ ቀጠናው በተካሄደው መርሃ ግብር ላይ ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን ከአረንጓዴ  አሻራ መረሃግብሩ በተጨማሪ በድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠና እየተከናወኑ ያሉ  የስራ እንቅስቃሴዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል ፡፡