• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 1 month ago
  • 337 Views

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የአምስተኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር መልዕክት

አረንጓዴ አሻራችንን ስናሳርፍ ጥላቻንና መገፋፋትን ወደጎን በመተው  አንድነትን፣ ፍቅርን፣ መተሳሰብንና አብሮነትን ሀገራዊ እሴት ለማድረግ እየሰራን መሆን አለበት - አክሊሉ ታደሰ 
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል ሀገራዊ መርሃ ግብርን በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ አስጀምረዋል። 

ዋና ስራ አስፈፃሚው መርሃ ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት ባደረጉት ንግግር በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር መገፋፋትንና ጥላቻን አስወግደን እንደ ሀገር የምንታወቅባቸውንና በርትተን ልንሰራባቸው የሚገቡንን እንደ አብሮነት፣ ፍቅር፤ ወንድማማችነት እንዲሁም የሀገር ፍቅር የመሳሰሉ ህብረብሔራዊ ማንነታችንን አግዝፈው የሚያሳዩ ተግባራት ላይ በማተኮር ለቀጣዩ ትውልድ ምቹና የበለፀገች ኢትዮጵያን የማስተላለፍ ኃላፊነት አለብን ብለዋል። 

በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሃ ግብር የራሳችን ሪከርድ የሚሰበርበትና የአፍሪካ አረንጓዴ ግንብ ንቅናቄ  መጀመሩ የሚበሰርበት ታላቅ ቀን መሆኑን አቶ አክሊሉ በመድረኩ ገልፀዋል። 

በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በተካሄደው በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሰራተኞች፣ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ኤጀንሲ፣ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኤጀንሲና ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር እንዲሁም የአቃቂ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች አመራርና ሰራተኞች ተገኝተዋል። 

የ5ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አክሊሉ ታደሰ እና የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሀጂ አወል አርባ በተገኙበት በሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ በይፋ የተጀመረ ሲሆን በመላ ሀገሪቱ በሚገኙት ኢንዱስትሪ ፓርኮች የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ ከ15 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ለመትከል ታቅዷል።