• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 2 months ago
  • 512 Views

በጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ወደ ኤሌክትሪክ ኢንጂን የሚቀይር ኩባንያ

በጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ወደ ኤሌክትሪክ ኢንጂን የሚቀይር ኩባንያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ገብቶ ለመስራት ያለውን ፍላጎት ገለፀ

በጋዝ የሚሰሩ ባለሶስት እግር እና ባለ አራት እግር ተሽከርካሪዎችን ወደ ኤሌክትሪክ ሲስተም የሚቀይር ኩባንያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ለመስራት ያለውን ፍላጎት ለኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገልጿል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ሰለሞን የኢንቨስትመንት ሀሳቡን ባለቤት ኢንጂነር እሸቱ መኮንንን ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን የኢንቨስትመንት ሀሳቡ ባለቤትም ስለ ኢንቨስትመንት እቅዱ ማብራሪያ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል። በውይይቱም ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ሽፈራው ኢንቨስትመንቱ እንደ ሀገር ያለው ጠቀሜታ ጉልህ በመሆኑ ኮርፖሬሽኑ ለኢንቨስትመንቱ መሳካት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

ኩባንያው በኡንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ግዙፍ የመገጣጠሚያ ወርክሾፕ በመክፈት በአንድ አመት ውስጥ 1 ሺ ባለ ሶስት እግር እንዲሁም 200 ባለ አራት እግር ተሽከርካሪዎችን ወደ ኤሌክትሪክ ሲስተም ለመቀየር የመጀመሪያ እቅድ አለው።

A company that converts gas-powered vehicles to electric engines has expressed interest to work in industrial parks.

A company that converts gas-powered three-wheeled and four-wheeled vehicles to electric systems has expressed its interest to work in industrial parks to IPDC.

IPDC Deputy CEO, Mr. Shiferaw Solomon welcomed the investor and discussed the investment plan with the investor. In the discussion, the Deputy CEO Mr. Shiferaw confirmed that IPDC will provide all the necessary support for the success of the investment as the investment has significant importance to the country.

The company has an initial plan to convert 1000 three-wheeled and 200 four-wheeled vehicles to electric systems within a year by opening a huge assembly workshop in industrial parks.