ኮሚሽኑ እና ኮርፖሬሽኑ በጋራ የተሳተፉበት መድረክ በፖርቹጋል ተካሄደ
የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሚ እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እንዲሁም ከፍተኛ አመራሮችና ከንቲባዎች የተሳተፉበት ውይይት በፖርቱጋል ሊዝበን ከተማ ተካሂዷል።
ውይይቱ የተካሄደው ከፖርቹጋል ውጪ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ፕሮፌሰር ዱቶር በርናርዶ ኢቮክሩዝ ጋር ሲሆን በውይይቱም ኢንቨስትመንትን የተመለከቱ ዝርዝር ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን በኢትዮጵያ ያሉ ዝርዝር የኢንቨስትመንት አማራጮችና ማበረታቻዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የሚመራ ቡድን አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን ወደ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለማምጣጥ ያለመ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በፖርቹጋል ሊዝበን እያደረገ መሆኑ ይታወቃል።
The forum in which EIC and IPDC participated together was held in Portugal
A discussion was held in Lisbon, Portugal, in which Investment Commission Commissioner Lelise Nemi and IPDC CEO Aklilu Tadesse including higher officials and mayors participated.
The discussion was held with foreign affairs Deputy Minister of portugal Prof Doutor Bernardo Ivo Cruz, and in the discussion, detailed issues regarding investment were raised, and detailed investment options and incentives in Ethiopia were presented.
A delegation led by IPDC CEO Aklilu Tadesse is in an official visit to Lisbon, Portugal with the aim of bringing new investments to industrial parks.