• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 5 months ago
  • 1030 Views

የመገናኛ ብዙሀን እና የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ሚና

ኢንቨስትመንትን በማስተዋወቅ እና በመሳብ የመገናኛ ብዙሀን እና የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ሚና ጉልህ መሆኑ ተገለፀ

ይህ የተገለፀው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክን ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን እና ለማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ባስጎበኘበት ወቅት ነው።

በጉብኝቱ ከ13 በላይ የሚሆኑ የመገናኛ ብዙሀን እንዲሁም የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን የፓርኩን ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ፣ የአምራች ኩባንያ የምርት ሂደትን እንዲሁም ለአምራች ባለሀብቶች የተዘጋጁ መሰረተ ልማቶችና አገልግሎቶችን ተመልክተዋል።

በጉብኝቱ ወቅትም የጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ሊኪሳ የፓርኩን ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ፣ የኩባንያዎችን የስራ ሂደት እንዲሁም ለባለሀብቶች ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችና የአካባቢውን እምቅ የተፈጥሮ ለጉብኝቱ ተሳታፊዎች በዝርዝር አብራርተዋል።

የጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ75 ሄክታር ላይ ያረፈ ግዙፍ የኢንቨስትመንት ማዕከል ሲሆን አምራች ኩባንያ በስራ ላይ እንዲሁም ሌላ ኩባንያ በግንባታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ወደ ፓርኩ ለመግባት ፍላጎት ያላቸው ኢንቨስተሮች ጥያቄዎቻቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ።

ኢንዱስትሪ ፓርኩ ካለው የተሟላ መሰረተ ልማት በተጨማሪ በአካባቢው የሚገኙት እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶች በተለይም የማር፣ የአቮካዶ እና የቡና ግብዓቶች ለግብርና ማቀነባበር ተመራጭ ቦታ ያደርገዋል።

The role of mass media and social media influencers in promoting and attracting investment is irreplaceable

This was stated when IPDC toured Jimma Industrial Park for local medias and social media influencers.

More than 13 local media and social media influencers participated in the your and visited current activities of the park, the production process of manufacturing company, and the infrastructure and services provided for manufacturing investors.

During the visit, Jimma Industrial Park Manager, Mr. Tesfaye Likisa, explained in detail the current activities of the park, the production process of companies, investment options for investors and the natural potential of the area to the participants of the tour.

Jimma Industrial Park is a huge investment center on 75 hectares, a manufacturing company is in operation and another investor is under construction and additional investors are submitting their requests to enter the park. In addition to the industrial park's state of the art infrastructure, the potential natural resources in the area, especially honey, avocado and coffee resources make it an ideal location for agro processing.