• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 2 months ago
  • 368 Views

ኮርፖሬሽኑ ባለፉት አስር ወራት ከባለድርሻ አካላት ጋር

ኮርፖሬሽኑ ባለፉት አስር ወራት ከባለድርሻ አካላት ጋር የነበረው ግንኙነት ላይ ያደረገው ሪፎርም ውጤት እያመጣ መሆኑ ተገለፀ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ባለፉት አስር ወራት ከባለድርሻ እና ከመገናኛ ብዙሀን አካላት ጋር ለአንድ አገራዊ አላማ ተቀራርቦ ለመስራት ያደረገው ሪፎርም ውጤት እያስመዘገበ መምጣቱን የኮርፖሬሽኑ ማርኬቲንግና ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘመን ጁነዲን ገልፀዋል።

ኃላፊው እንዳሉት ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ ከንግድ ሚኒስቴር፣ ከስተም፣ የየክልል የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከፍተኛ የትምህርት ተቋት እና የመገናኛ ብዙሀን ዋናውን ድርሻ እንደያዙ ጠቁመዋል።

ኮርፖሬሽኑ የተቋቋመበትን አላማና ራዕይ ማሳካት እንዲችል እንዲሁም በሀገሪቱ በተለይም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለውን እምቅ የኢንቨስትመንት አማራጭ በማስተዋወቅ በኩል የመገናኛ ብዙሀን እና የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ያላቸው ሚና የማይተካ መሆኑን የገለፁት አቶ ዘመን ኮርፖሬሽኑ በቀጣይም ከባለድርሻ አካላት፤ በተለይም ከመገናኛ ብዙሀን እና ከማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ጋር በትብብር መስራት እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

ዛሬም ኮርፖሬሽኑ ከጅማ ከተማ አመራሮች፣ የመገናኛ ብዙሀን አባላት እና እውቅ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች፣ ከከተማው ማህበረሰብ ጋር በጋራ በመሆን በጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አከናውኗል።

የጅማ ከተማ ኃላፊዎችን ጨምሮ ከ13 በላይ የሚሆኑ መገናኛ ብዙሀን አባላት እንዲሁም እውቅ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ከፓርኩ አመራርና ሰራተኞች እንዲሁም ከአካባቢው ማህበረሰብ አካላት ጋር 5ተኛውን ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ አከናውነዋል።

ተሳታፊዎች በመርሀ ግብሩ ሀገር በቀልና ለምግብነት የሚውሉ ችግኞች ተክለዋል።

በጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ቋሚ የአረንጓዴ ልማት ቡድን ያለው ፓርክ ሲሆን በ5ተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርም ከ80 ሺ ችግኞች በፓርኩ እንደሚተከሉ በመርሀግብሩ ተገልጿል።

ቀደም ሲል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በኮርፖሬሽኑ 5ተኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር 15 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ፕሮግራሙን በይፋ ማስጀመራቸው አይዘነጋም ።