የፖርቹጋል ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ምዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ተጠየቀ
የፖርቹጋል ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና በዘርፈ ብዙ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሰማሩ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ጥሪ አቅርበዋል
ዋና ስራ አስፈፃሚው ጥሪውን ያቀረቡት ከልዑካቸው ጋር በኢትዮጵያ የፖርቹጋል አምባዳሰር ከሆኑት ሉዊዛ ፍራጎሶ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።
በውይይታቸውም ኢትዮጵያና ፖርቹጋል በኢንቨስትመንት፣ በኢኮኖሚ እና በሌሎች የትብብር መስኮች ያላቸውን ግንኙነት አጠናክረው መቀጠል በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።
በቀጣይም ሁለቱ አገራት በተለይም የኢንቨስትመንት ግንኙተታቸው ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የፖርቹጋል ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና በዘርፈ ብዙ ኢንቨስትመንቶች እንዲሰማሩ ለማድረግ ስራዎች እንዲሰሩ ከመግባባት ተደርሷል።