• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 5 months ago
  • 996 Views

5ተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን 5ተኛ ዙር አረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በአፋር ክልል በሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ በይፋ ተጀመረ

እንደ ሀገር 'ነገን ዛሬ እንትከል' በሚል መሪ ቃል የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ሁለተኛው ምዕራፍ አካል የሆነው የኮርፖሬሽኑ 5ተኛ ዙር የአርንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በአፋር ክልል በሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ በይፋ ተጀምሯል።

መርሀ ግብሩን የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የአፋር ክልል ፕሬዚዳንት ክቡር ሀጂ አወል አርባን ጨምሮ የሰመራ ከተማ ከንቲባና ሌሎች የክልሉና የከተማው ከፍተኛ አመራሮች፣ የኮርፖሬሽኑ የማኔጅመንት አባላት፣ በኢንዱስትሪ ፓርኩ ኢንቨስት የሚያደርጉ ባለሀብቶች በተገኙበት አስጀምረዋል።

መርሀ ግብሩን በይፋ ያስጀመሩት ዋና ስራ አስፈፃሚው አክሊሉ ታደሰ በአረንጓዴ አሻራ እንደ ሀገር የተጣለብንን ኃላፊነት ለመወጣት በሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ያስጀመርነውን መርሀ ግብር በሁሉም ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና እና በየአካባቢው ካሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በመተባበር 15 ሚሊየን ችግኞችን እንተክላለን ብለዋል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በአምስተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ለምግብነት የሚውሉ አገር በቀል ችግኞችን ጨምሮ 15 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በሁሉም ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና የሚተክል ይሆናል።

The 5th Round Green Legacy Program of IPDC was officially launched at Samara Industrial Park in Afar Region.

As a part of the second phase of the National Green Legacy program, which was launched with the slogan 'Lets Plant Our Future Today', the 5th round of the Corporation's Green Legacy Program has been officially launched at Samara Industrial Park in Afar region.

The program was launched by IPDC CEO, Aklilu Tadesse, in the presence of the president of Afar region, Honorable Haji Awol Arba, the mayor of Semera city, other senior leaders of the region and the city, the management members of IPDC, and investors investing in the industrial park.

The CEO said that in order to fulfill our responsibility as a corporation with Green Legacy , we will continue the program that we started today at Semara Industrial Park in all industrial parks and Dire Dawa Free Trade Zone to plant 15 million plants.

In the 5th round of the Green Legacy Program, Industrial Parks Development Corporation will plant 15 million indigenous plants including edible ones in all industrial parks and Dire Dawa Free Trade Zone.