• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 2 months ago
  • 378 Views

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚደንት ሀጂ አወል አርባ መልዕክት

የሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክን ለኢንቨስትመንት ይበልጥ ተመራጭ የሚያደርገው የጅቡቲ ፤የ ታጁራ እና የአሰብ ወደብን በቅርብ ርቀት ለመጠቀም የሚያስችል ኮሪደር መሆኑ ነው - የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚደንት ሀጂ አወል አርባ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን 5ተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርን የክልሉ ፕሬዚዳንት ፤ ከፍተኛ አመራሮች ፤ ኢንቨስተሮች እና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት በአፋር ክልል በሰመራ ከተማ በይፋ አስጀምሯል።

በመርሀ ግብሩ ንግግር ያደረጉት የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት ሃጂ አወል አርባ ክልል ላይ ጥቁሩም ነጩም ፤ አፋሩም ሌላውም የየትኛውም ቦታ ሀገር ሰው ኢንቨስት ቢያደርግ የክልላችን አንድ አካል አድርገን ተቀብለን ተንከባክበን እንቀበላለን ብለዋል።

ሰመራ የጅቡቲ ፤ የታጁራ እና አሰብ ወደብን ለመጠቀም የሚያስችል ኮሪደር መሆኑ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ቦታ እንደሚያደርገውም ነው ፕሬዚደንቱ የገለፁት።

ፕሬዚዳንቱ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርን በአፋር ክልል ሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ በማድረጉ ክብር ይሰማናል ብለው በአጋጣሚው ሶስት ተጨማሪ ባለሀብቶች ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ ኮርፖሬሽኑ ላደረገው አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል።