• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 5 months, 1 week ago
  • 352 Views

የዋና ስራ አስፈፃሚው መልዕክት

"በኢንዱስትሪ ፓርኮቻችን የቻይናውያን ባለሀብቶችን ተሳትፎ ይበልጥ ለማሳደግ እየተሰራ ነዉ" - አክሊሉ ታደሰ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ኮርፖሬሽናቸው በሚያስተዳድራቸው አለም አቀፍ ደረጃቸውን በጠበቁ ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ነፃ ንግድ ቀጠና የቻይናውያን ባለሀብቶችን ተሳትፎ በይበልጥ ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ገለፁ።

አቶ አክሊሉ ይህን የገለፁት ከቻይና ሁናን ግዛት ለመጡ የተለያዩ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ስላሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዝርዝር ገለፃ ባደረጉበት መድረክ ላይ ነው።

በመድረኩ ከቻይና ሁናን ግዛት የመጡና በአግሮ ፕሮሰሲንግና ማዕድን ዘርፍ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት ካላቸዉ የቻይና ባለሀብቶች ጋር ኢንቨስትመንት ተኮር ዉይይት ተካሂዷል።

በዉይይቱም በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከል ያለውን ጠንካራ የኢንቨስትመንት ግንኙነት ይበልጡን ለማሳደግና ለማጠናከር የሚያስችሉ ጉዳዮች አፅንኦት ተሰጥቶባቸዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ አክሊሉ ታደሰ ኮርፖሬሽኑ ከዚህ ቀደም ትኩረት ካደረገባቸው የኢንቨስትመንት ዘርፎች በተጨማሪ በተለይም በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ መሰማራት ለሚፈልጉ ቻይናውያንና ሌሎችም ባለሀብቶች አላስፈላጊ ቢሮክራሲን በማስቀረትና Zero Waiting Bureaucracy አገልግሎት አሰጣጥ ተግባራዊ በማድረግ በፈጣን መንገድ ለማስተናገድ መዘጋጀቱን አሳውቀዋል።

"We are working with commitment to increase the participation of Chinese investors in our industrial parks" - Aklilu Tadesse

Industrial Parks Development Corporation CEO, Aklilu Tadesse, said that efforts are being made with higher commitment to further increase the participation of Chinese investors in the world-class industrial parks and free trade zone managed by his corporation.

Mr. Aklilu said this at a forum where a detailed explanation of investment options was given for various companies from China Hunan province.

At the forum, an investment-oriented discussion was held with Chinese investors who came from China's Hunan Province and are interested in participating in the agro-processing and mining sector.

In the discussion, issues that can further increase and strengthen the strong investment relationship between Ethiopia and China were emphasized.

Speaking at the forum, IPDC CEO Aklilu Tadesse announced that in addition to the areas of investment that IPDC has focused on in the past, especially Chinese and other investors who want to engage in the agro processing sector, by avoiding unnecessary bureaucracy and implementing Zero Waiting Bureaucracy service delivery, IPDC is prepared to accommodate in a very effective way.

#Invest_In_Zero_Waiting_Time_Bureaucracy