• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 8 months, 1 week ago
  • 490 Views

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን የሚያመርተው የቻይናው ኩባንያ

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን የቻይና ኩባንያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገለፀ 

በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የተለያዩ አይነት የሁለት እግር ተሽከርካሪዎችን እና ስኩተሮችን የሚያመርት ያዲያ የተሰኘ ዓለም አቀፍ የቻይና ኩባንያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳለው ለኮርፖሬሽኑ ገልጿል። 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን እና ማርኬቲንግ ዘርፍ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘመን ጁነዲን የኩባንያውን ዋና ስራ አስኪያጅና ከፍተኛ ኃላፊዎች ተቀብለው አነጋግረዋል። 

የኩባንያው ኃላፊዎች ስለ ኩባንያው ፤ ስለ ኢንቨስትመንት እቅዱ እንዲሁም ኩባንያው ያለበትን ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ አስመልክተው ገለፃ ያደረጉ ሲሆን  በፓርኮች ስላሉ መሰረተ ልማቶች ፤ የአገልግሎት አሰጣጥና ማበረታቻዎችን የተመለከቱ ተያያዥ የኢንቨስትመንት ጉዳዮች ጭምር  ውይይት ተደርጎባቸዋል። 

ምክትል ስራ አስፈፃሚው አቶ ዘመን  ኩባንያው የተሰማራበት የኢንቨስትመንት ዘርፍ እንደ ሀገር ባለፉት አምስት ዓመታት እየተተገበረ ካለዉና በአጭር ጊዜ ዉጤታማ ከሆነዉ የአረንጓዴ ልማት ስራ ጋር ተመጋጋቢ መሆኑን አንስተዉ ለኢንቨስትመንቱ መሳካት ኮርፖሬሽኑ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። 

መቀመጫውን ቻይና ያደረገው ያዲያ ኩባኒያ  እ.አ.አ በ2001 የተመሰረተ የተለያዩ ባለ ሁለት እግር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለአለም ገበያ የሚያቀርብ  ሲሆን ምርቶቹን ከ100  በላይ ለሚሆኑ ሀገራት የሚያቀርብ ፤ በሽያጭ መጠን ላለፉት ስድስት ዓመታት ቁጥር አንድ የሆነ እና አረንጓዴ ከባቢን የሚያበረታታ ግዙፍ አምራች ኩባንያ ነው። 

A Chinese company that produces electric vehicles expressed its desire to invest in industrial parks 

Yadea, an international Chinese company that manufactures different types of electric two-wheel vehicles, has expressed to IPDC that it is interested in investing in industrial parks. 

Industrial Parks Development Corporation  Investment Promotion and Marketing Deputy CEO, Mr. Zemen Junedin received and spoke to the company's General Manager and senior officials. 

The Company Officials made a statement about the Company, the investment plan and the company's current activities and discussion was held. 

IPDC,s Deputy CEO Mr. Zemen appreciated  the company's interest in investment and stated that the investment has great importance to the corporation and to the realization of the country's green development plan. He additionally assured that the corporation will support the success of the investment. 

Established in 2001 and Based in China, Yadea is a company that supplies two-wheeled electric vehicles to the world market, and supplies its products to more than 100 countries. Yadea is a giant manufacturer that has been number one in terms of sales volume for the past six years and promotes a green environment.

#invest_in_zero_waiting_time_bureaucracy