የሩሲያ ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢንቨስት እንዲያደርጉ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ነፃ ንግድ ቀጠና አዳዲስ የሩሲያ ባለሀብቶች ኢንቨስት እንዲያደርጉ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ከሆኑት ኢቭጌኒ ቴሬሂን ጋር ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱም የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ ያላቸውን ረጅምና በፈተና ያልደበዘዘ ጠንካራ ወዳጅነት የሚመጥን የኢንቨስትመንት ግንኙነት እንዲኖራቸው መስራት እንደሚያስፈልግና ለዚህም ኮርፖሬሽኑ ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ቴሬሂን በበኩላቸው ኤምባሲያቸው አዳዲስ የሩሲያ ባለሀብቶች በግብርና ፤ በአዉቶምቢል አሴምብሊና ሌሎችም የማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ኢንቨስት እንዲያደርጉ በስፋት እየሰራ መሆኑን አስታውሰዋል። በቅርቡም በድሬዳዋ የነፃ ንግድ ቀጠናና ሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለመግባት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ኢንቨስተሮች መኖራቸውን የጠቆሙት አምባሳደሩ በኢንዱስትሪ ፓርኮቹ የቀረቡ ስታንዳርድ መሰረተ ልማቶች ለኢንቨስተሮቹ ምቹ መሆናቸውንና በጋራ በመስራት ትልቅ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል አሳውቀዋል።
በኤምባሲው እና ኮርፖሬሽኑ መካከል ከተደረገው ኢንቨስትመንት ተኮር ውይይት ጎን ለጎን የኮርፖሬሽኑን አመራሮችና ሰራተኞች ሁለንተናዊ አቅም ለማሳደግ አጫጭርና የረጅም ጊዜ የትምህርትና የስልጠና ፕሮግራሞች በሚመቻቹበት አግባብ ላይ ከስምምነት ተደርሷል ።
Russian embassy is working eagerly to enable Russian investors to invest in Industrial Parks
It is stated that Russian embassy is working eagerly to enable Russian investors to invest in Industrial Parks and free trade zones managed by IPDC.
Industrial Parks Development Corporation CEO, Aklilu Tadesse had a discussion with Evgeny Terekhin, who is the ambassador of Russia in Ethiopia.
IPDC CEO, Aklilu Tadesse, stated in the discussion that it is necessary to work for an investment relationship that suits the long and strong friendship between Ethiopia and Russia, and for this he confirmed that the corporation is more ready than ever.
Evgeny Terekhin, the Russian ambassador to Ethiopia, reminded that his embassy is working for new Russian investors to invest in industrial parks. The ambassador, additionally pointed out that there will be investors coming to Ethiopia soon, and he has visited the Hawassa Industrial Park and informed that the standard infrastructure provided in the park is convenient for the investors.
Along with the investment-oriented discussion, there was a discussion on possible ways in which short and long education and training programs can be arranged to increase the overall capacity of the corporation's leaders and employees.