• Addis Ababa
    Sun:Jan:2026 11:06:18pm
  • Madrid
    Sun:Jan:2026 09:06:18pm
  • Paris
    Sun:Jan:2026 09:06:18pm
  • Beijing
    Mon:Jan:2026 04:06:18am

Employee Guiance


IPDC Guidance

Mountains

አጠቃላይ የጭንቀት በሽታ

በሕይወት ስንኖር በአንዳንድ አጋጣሚዎች የተነሣ መጠነኛ የሆነ መጨነቅ ወይም መረበሽ ሊገጥመን ይችላል። ይህ የተለመደ እና ጤናማ ነው። ነገር ግን አጠቃላይ የጭንቀት በሽታ (GAD) የአለባቸው ሰዎች ከእውነታው በራቀ ወይም ከሚገጥማቸው ችግር ጋር በአልተመጣጠነ መልኩ ፍርሃት እና ጭንቀት ይታይባቸዋል። እነዚህ ሰዎች አብዝተው ስለ ጤና፣ ገንዘብ፣ ቤተሰብ፣ ሥራ ወይም ትምህርት ይጨነቃሉ። መረበሻቸውንም በቀላሉ ማቆም አይችሉም ፡፡ Read More

Lights

የመካንነት መድኃኒቶች

ለመካንነት የሚሰጡ መድኃኒቶች እና ሕክምናዎችን የሚወስዱ ሴቶች፤ በማኅፀን ውስጥ የሚቀመጥ የእርግዝና መከላከያ (IUD) የሚጠቀሙ ሴቶች የማርገዝ ዕድላቸው እጅግ አነስተኛ ነው፡፡ ሆኖም እርግዝና በሚፈጠርበት ጊዜ ግን ከማኅፀን ውጪ የመሆን ዕድሉ ከፍተኛ ይሆናል፡፡ በማኅፀን ውስጥ እያሉ ለ ዲኢታይልስቲልቢስትሮል (diethylstilbestrol) (ተፈጥሮአዊ የአልሆነ ሰው ሠራሽ /ሲንቴቲክ/ ለሴቶች የሚታዘዝ ኢስትሮጅን ሆርሞን ነው፡፡ Read More

Nature

የአዕምሮ ጤንነት

ከሚከተሉት ምልክቶች አንዱ ከተገኘ እርዳታ ይጠይቁ፡ አሁን ያለኝ ስሜት ህይወቴን በተለመደው መንገድ እንዳላከናውን ከለከለኝ። የምኖረውን ወይም አብሬያቸው የምሠራውን ሰዎች አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረኩ እንደሆነ ይሰማኛል። ስሜቴ ለብዙ ሳምንታት እየተለወጠ ነው። ራሴን የመጉዳት ወይም ሌሎችን የመጉዳት ሃሳቦች አሉኝ። በሥራ ቦታ፣ ወይም የቤት ውስጥ ሥራ በምሠራበት ጊዜ፣ ከወትሮው የበለጠ ድካም ይሰማኛል፣ ወይም ያልተለመዱ ስህተቶችን አደርጋለሁ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራሴን ማግለል እመርጣለሁ። Read More

Mountains

ደስታን ለመፍጠር የሚረዱ መንገዶች

በቀን ቢያንስ የ10 ደቂቃ ፅሞና ማድረግ ይኖርብናል። ፅሞና ማድረግ ሙሉ ትኩረትን በመሰብበስብ ለአፍታ ከራስ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ቀጣይ በምን ነገሮች ላይ ደስታን ማምጣት እንደሚቻል መንገዱን ክፍት አድርጎ ያሳያል። በህይዎታችን ቅድሚያ የምንሰጣቸውንና ጤናማ ግንኙነት ካለን ሰዎች ጋር ጊዜ ሰጥተን ማውራትና መጫወት ተጨማሪ ደስታ ያመነጫል። Read More

Bear

የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን

የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የሽንት ስርአት አካላትን ማለትም (ኩላሊትን ፣ የሽንት ፊኛን እና የላይኛውን (Ureter ) እና የታችኛውን (urethra ) የሽንት ማስተላለፊያ ቱቦዎች የሚያጠቃ የኢንፌክሽን አይነት ነው። ብዙዎቹ ኢንፌክሽኖች የታችኛውን የሽንት ቧንቧዎች (Urethra ) እና የሽንት ፊኛንና (Urinary Bladder ) ያጠቃሉ። ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ለበሽታው ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው። ኢንፌክሽኖች ከ ሽንት ፊኛ አልፈው ወደ ኩላሊት ከተሻገሩ አሳሳቢ የጤና እክል ሊያስከትሉ ይችላሉ። ሃኪሞች የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽንን አንቲባዎቲክ (ፀረ ህዋስ) መድሃኒቶች በመስጠት ያክማሉ። ነገር ግን በሽታው ቀድሞ ሳይከሰት ራስን ከሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን መጠበቅ ከበሽታው ጋር ተያይዘው ሊመጡ የሚችሉ ጉዳቶችን ለመቀነስ ይጠቅማል ። የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ምልክቶች ምንድናቸው አንዳንዴ ምልክት ላያሳይ ይችላል ፤ ካሳዩ ግን ምልክቶቹ እነዚህን ይመስላሉ። በመጠን አነስተኛ ግን በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት ደመናማ የመሰለ የሽንት ከለር የሽንት ከለር መቀየር – ቀይ፣ ሮዝ ወይም ጠቆር ያለ ሽንት —ከሽንት ጋር የደም ምልክት ያልተለመደ ጠንከር ያለ የሽንት ሽታ ማህፀን አካባቢ የሚሰማ የመጫን ህመም (ለሴቶች) ወይም ወንዶች ብልታቸው አከባቢ እና የሽንት ፊኛ አከባቢ የሚሰማ ህመም



UP