የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የሽንት ስርአት አካላትን ማለትም (ኩላሊትን ፣ የሽንት ፊኛን እና የላይኛውን (Ureter ) እና የታችኛውን (urethra ) የሽንት ማስተላለፊያ ቱቦዎች የሚያጠቃ የኢንፌክሽን አይነት ነው። ብዙዎቹ ኢንፌክሽኖች የታችኛውን የሽንት ቧንቧዎች (Urethra ) እና የሽንት ፊኛንና (Urinary Bladder ) ያጠቃሉ።
ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ለበሽታው ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው። ኢንፌክሽኖች ከ ሽንት ፊኛ አልፈው ወደ ኩላሊት ከተሻገሩ አሳሳቢ የጤና እክል ሊያስከትሉ ይችላሉ።
ሃኪሞች የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽንን አንቲባዎቲክ (ፀረ ህዋስ) መድሃኒቶች በመስጠት ያክማሉ። ነገር ግን በሽታው ቀድሞ ሳይከሰት ራስን ከሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን መጠበቅ ከበሽታው ጋር ተያይዘው ሊመጡ የሚችሉ ጉዳቶችን ለመቀነስ ይጠቅማል ።
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ምልክቶች ምንድናቸው
አንዳንዴ ምልክት ላያሳይ ይችላል ፤ ካሳዩ ግን ምልክቶቹ እነዚህን ይመስላሉ።
በመጠን አነስተኛ ግን በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት
ደመናማ የመሰለ የሽንት ከለር
የሽንት ከለር መቀየር – ቀይ፣ ሮዝ ወይም ጠቆር ያለ ሽንት —ከሽንት ጋር የደም ምልክት
ያልተለመደ ጠንከር ያለ የሽንት ሽታ
ማህፀን አካባቢ የሚሰማ የመጫን ህመም (ለሴቶች) ወይም ወንዶች ብልታቸው አከባቢ እና የሽንት ፊኛ አከባቢ የሚሰማ ህመም